የእለት ዜና

የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ለወሰኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች በመስቀል አደባባይ ሽኝት ተደረገላቸው

የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ለወሰኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች በመስቀል አደባባይ ሽኝት ተደረገላቸው።

“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ”!! በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡና የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ለወሰኑ ወጣቶች የሽኝት መርሐግብር ዛሬ ማለዳ ላ ተከናውኗል።

በማለዳው በመዲናዋ ከየአቅጣጫው የተውጣጡ በርካታ ዘማች ወጣቶች በመስቀል አደባባይ ተገኝተዋል።

በስንቅ ድጋፍ፣ ደም በመለገስና መሰል እንቅስቃሴዎችም የከተማዋ ህዝብ ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

አባት አርበኞች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ለዘማቾቹ የአገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ ያሳዩትን ቁርጠኝነት በማድነቅ ይህንን ስራቸውን አገራቸው ከፍ አድርጋ እንደምትዘክረው በመግለፅ መርቀውም ሸኝተዋቸዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!