የእለት ዜና

ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ተበጀላቸው

የ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ላይ ትምህርት ቤቶች ክፍያ እንዴት መጨመር እንዳለባቸው መመሪያ ተዘጋጅቶ ለትምህርት ቤቶች መሰጠቱን በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ አስታወቁ፡፡

መመሪያው ትምህርት ቤቶቹ ጭማሪ ክፍያ ምን ምን ላይ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስቀምጥ ሲሆን ትኩረት የሚያደርግበት እና የሚወስነው ግን የምዝገባ ክፍያን መገደብ ላይ ብቻ ነው ብለዋል፡፡ የገንዘብ ምጣኔው 25 በመቶ ጭማሪ እንዲደረግበት መወሰኑንም አያይዘው ገልፀዋል፡፡

በምዝገባ ክፍያ ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈለገው ትምህርት ቤቶች ለመመዝገቢያ ክፍያ የሚጠይቁት ገንዘብ ከፍተኛ ስለነበረ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ ስምምነቱ በትምህርት ቤቶች እና በወላጆች መካከል እንደሚሆንና ተቋማቸው ጣልቃ እንደማይገባ ምክትል ስራ አስኪያጇ ያሳወቁ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹ በሚያስቀምጧቸው በቂ ምክንያች እና ከወላጆች ጋር በመተማመን ይወሰናል ማለታቸውን አሓዱ ዘግቧል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!