የእለት ዜና

መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ ለህብረተሰቡ እንዳያደርስ የሕወሃት ቡድን እንቅፋትእየሆነበት ነው፡- ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ ለህብረተሰቡ እንዳያደርስ የሕወሃት ቡድን እንቅፋትእየሆነበት እንደሚገኝ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲርደስ ለማስቻል አልሞ ያደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ መደናቀፉን ቀጥሏል ሲል ገልጿል።

መንግስት በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ውስጥ ከ400,000 ኩንታል የሚበልጥ ስንዴ እና ከ2.5 ሚሊዮን ሊትር የሚበልጥ የምግብ ዘይት አከማችቶ ማስቀመጡም ተገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል ያሉት ዜጎቻችን ደህንነት የኢትዮጵያን መንግሥት እንደሚያሳስበው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪው አስታውቋል።

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በተለይም ደግሞ በትግራይ ድጋፍ በመስጠት ላይ የሚገኙት፣ ህወሓት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አቁሞ ሰብዓዊ እርዳታ ለያዙ ተሽከርካሪዎች መንገዱን እንዲከፍት ግፊት ማሳደር አለባቸው ሲልም አሳስቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!