የእለት ዜና

በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት የፊታችን ዓርብ እንደሚጠናቀቅ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ

በትግራይ ያለው የምግብ ክምችት የፊታችን ዓርብ እንደሚጠናቀቅ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊይ በቲውተር ገጻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ በትግራይ የምግብ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እርዳታውን ለማቅረብ በቀን 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በአሁኑ ወቅት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ 170 ተሽከርካሪዎች አፋር ላይ መቆማቸውን እና መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ሰዎች ለምግብ እጥረት እየተጋለጡ ነው፤ ስለዚህ እነዚህ ተሸከርካሪዎች አሁኑኑ እንዲንቀሳቀሱ ሊፈቀድላቸው ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!