የእለት ዜና

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማሕበር በጊዜያዊ ማቆያ ላሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

በሳዑዲ አረቢያ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማሕበር አባላት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በጊዜያዊ ማቆያ ላሉ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ የተደረገው በሪያድ በዋፊዲን አስተዳደር ስር በሚገኘው “ነዚም የሴቶች ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል” ለሚገኙ 1221 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሲሆን የምግብ፣ ወተት፣ ውሃ፣ አልባሳት፣ የሴቶችና ህጻናት ንጽህና መጠበቂያና ሌሎችም የፍጆታ እቃዎች ድጋፍ ማድረጉን ኤምባሲው አስታውቋል።

ለወገን ደራሹ ወገን ነው በሚል እሳቤ በመመራት በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር አስተባባሪነት ለተቸገሩ ወገኖች ለተደረገው ድጋፍ አስተዋፆ ላደረጉ ኮሚኒቲ አባላት ኤምባሲው ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!