የእለት ዜና

ከ8 ሺህ በላይ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች በ2013 በጀት ዓመት መቅረባቸው ተገለፀ

በ2013 በጀት ዓመት በፌደራልና በክልሎች ደረጃ 8 ሺህ 181 የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች ለፍትህ አካላት መቅረባቸውን በሪፖርት መመላከቱን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ያጠናቀረው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች እና ዓቃቤ ሕግ ተቋማት ሪፖርት እንደሚያመለክተው በ2013 በጀት ዓመት ከፌደራል እስከ ክልሎች ድረስ በየደረጃው ባሉት የፍትህ አካላት 6 ሺህ 98 መዝገቦች በፖሊስ ኮሚሽኖች ተመርምረው ለዓቃቤ ሕግ ተቋማት ተላልፈዋል ብሏል፡፡

ከነዚህ ውስጥ በ1 ሺህ 728 የክስ መዝገቦች ላይ ውሳኔ መሰጠቱንም አስታውቋል፡፡

በፌደራል ደረጃ በ969 መዝገቦች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔዎች ተላልፈው በ646 መዝገቦች የተከሰሱ የሙስና ወንጀል ፈጻሚዎች ላይ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት የተላለፈ ሲሆን ሌሎች በሂደት ላይ እንደሚገኙ ሪፖርቱ ማሳቱን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!