የእለት ዜና

የዓለም አካባቢ ቀን ከPHE ኢትዮጵያ ኮንሶርትየም ጋር ሲከበር

ፒ.ኤች.ኢ ኢትዮጵያ ኮንሶርትየም የተቀናጀ አሰራርን ለማስተዋወቅ እና በስፋት እንዲተገበሩ በማድረግ የሰዎች እና የአካባቢ መስተጋብር ተጠጥሞ ዘላቂ ልማትን እውን ርዕይን አንግቦ በ2000 ዓ.ም የተመሰረት ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የአካካቢ፣ የሥነ-ሕዝብ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚ እና የጤና ጉዳዮችን ያቀናጁ የተለያዩ የልማት ሥራዎች ሲያከናውን ቆያቷል።
በዚህ ገጽ ላይ የተካተቱት የተለያዩ አካላት ሐሳቦች የፒኤችኢ ኢትዮጵያን አቋም ላያንጸባርቁ ይችላሉ።

ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ የሄደውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት የሰው ልጅ ቆም ብሎ ስለ አካባቢ እንዲያስብ የሚያደርጉ ሀሳቦች ተቀርጸው የዛሬ 48 ዓመት በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሰኔ 5 ቀን 1972 የዓለም አከባቢ ቀን መከበር ጀመረ።
ኢትዮጵያም ይህንኑ ቀን ከ20 ዓመታት በኋላ በአገር አቀፍ ደረጃ ማክበር ጀመረች።

የአረንጓዴ አሻራ እንደ አንድ የአካባቢ መብት ነው ብሎ የሚመለከተው population health and environment consortium (PHE) ተቋም አንዱ ነው።
ዘንድሮ ግንቦት 28 ቀን PHE ኢትዮጵያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በካፒታል ሆቴል በከፍተኛ የምክክር መድረክ ውይይት አክብሯል።
በአሉን በበይነ መረብ ከሃዋሳ በንግግር የከፈቱት ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ናቸው።

የ2013 የአካባቢ ቀን ስናከብር ኹሉም ሰው የአረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ የአገራችንን ሥርዓተ ምህዳር እንዲያገግምና የተፈጥሮ ሚዛን እንዲጠበቅ ለአገራዊ ልማት ግብ መሳካት መሆኑ በአሉን ለየት ያደርገዋል ብለዋል።
የዘንድሮ መሪ ቃል ሥርዓተ ምህዳር ማገገም የሚረጋገጠው በአካባቢ ልማት ጥበቃና ዘላቂ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ሥራ ሲሠራ በመሆኑ አጠቃላይ የሰው ልጆች ማለትም የዛሬውንና የመጪውን ትውልድ የእለት ተዕለት ፍላጎትን ማሟላት እንዲቻል የምድር ላይ ሕይወትን ቀጣይነት በማበርከት ረገድ የሚኖረው ሚና ታሳቢ ባደረገ መልኩ ግንዛቤ መፍጠር የሚገባው የአለም አካባቢ ቀን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገራችንን ሥረዓተ ምህዳር ማገገም በተቀናጀ መልኩ ለመምራት የተባበሩት መንግስታት ለ10 ዓመት የሚቆይ UN decade Eco system restoration እቅድ ባሳለፍነው ዓመት ያስተዋወቀ ሲሆን፣ የዘንድሮ የዓለም አካባቢ ቀን የዚህን የረጅም ጊዜዕእቅድ የትግበራ ምዕራፍ የሚያበስር ቀን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት መሆኑን የገለጹት የUNFPA የኢትዮጵያ ተጠሪ ዴይና ግየል ናቸው።
ዴይና ግየል በንግግራቸው ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ ስጋት በመሆኑ ይህን ስጋት ለመቅረፍ የድርጊት መርሃ ግብር ቀርጸን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም የአካባቢ ፖሊሲ በመቅረጽና የ10 ዓመት ዕቅድ በመንደፍ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን ለመተግበር እየሰራ ይገኛል።የአየር ንብረት ለውጥ በማሕበረሰቡ ላይ የሚያሳድረው ጫና ብዙ ነው የሚሉት ዴይና ግየል የንጹህ ውሃ ችግር፣ለምግብ ዋስትና ስጋት፣ በተበከለ አካባቢ መኖር፣ የጤና እና የትምህርት አቅርቦትን ሊፈታተን ይችላል ብለዋል። እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ አጥኚዎች፣ የልማት አጋሮች እና መንግሥታት በጋራ ሊሰሩ ይገባል።

PHE ኢትዮጵያ ከተለያዮ የውጭ ድርጅቶች እና ከኢፌድሪ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ጋር በመሆን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ቀንን አክብሯል። በPHE አስተባባሪነት በዕለቱ ለአየር ንብረት ለውጥ መንስኤ ናቸው የተባሉ እና መፍትሄዎቻቸውን የሚዳስሱ የተለያዩ ጥናቶች ቀርበዋል።

በሥነ ህዝብ ጤና እና አካባቢ የሚሰራው PHE ኢትዮጵያ ኮነሰርቲም መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ተክሉ ገልጸዋል።
PHE ከተመሰረተ በፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ ለሕብረተሰቡ ዘላቂ የልማት አቅጣጫዎች መፍትሄ የማምጣት ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል። ይህ ደግሞ ከአፍሪካ በሕዝብ ብዛት በ2ኛ ደረጃ የምትገኝ ኢትዮጵያን የሥነ ሕዝብ ሂደቱን ከልማታችን ጋር በማስታርቅ ለውጦችን ለማምጣት እየሰራ የሚገኝ እንደሆነ ነው አቶ ነጋሽ የገለጹት።

PHE ሥነ ሕዝብ፣ጤና እና የኢኮኖሚ ልማት የማቀናጀት ሥራን ይሰራል። ይህ ሥራ ሲሰራ የተፈጥሮ ቦታዎች መነሻ በማድረግ ነው። PHE በብዛት የሚሰራባቸው ቦታዎች ጥብቅ የሆኑ፣ ተፋሰስ ቦታዎች፣ ደረቅ ቦታዎች እና የደን አካባቢዎችን መነሻ በማድረግ ነው።ከዚህ አንጻር ሰሜን ፓርክ፣ አዋሽ ፓርክ፣ መንዝ ጓሳ ኮሚኒቲ ሴንትራል ስምጥ ሸለቆ፣ ከጅማ ጀምሮ እስከ ኢሉአባቡራ ያሉ ቦታዎች ላይ PHE አመራር እየሰጠ፣ ከአባላቶችና አጋሮች ጋር በመሆን በተፈጥሮ ሥራ ሕብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ አዳዲስ ፕሮጀክት ሰርቷል ተብሏል።

ተራራማ አገር እንደመሆኗ መጠን ከተራሮቹ የሚወጣው አፈር ኃይቆቻችን እየጎዱ ይገኛሉ።
በምዕራብና በምስራቅ፣ በከፍተኛ እና ዝቅተኛ ቆላ ቦታ ላይ ያሉትን ኃይቆች እንዴት ማዳን እንደሚቻል ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሰንቀሌ፣ የአብያታ ሻላ እና ባሌ ተራሮች ላይ ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ቦታዎችን በመለየት ተፈጥሮዎችን ለማዳን ጥረት ማደረግ እንደሚገባ ነጋሽ ይገልጻሉ።
ይህንንም መሰረት በማድረግ የአካባቢ ጥበቃ መብትን በተመለከተ PHE ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ በመሆን የተለያ ባለ ድርሻ አካላት አባል የሆኑበት ገር አቀፍ ፕላትፎረም አቋቁሟል።
PHE ከጀመረው ስራ አንዱ የሆነውን ጋዜጠኞችን በማስተባበር የአየር ንብረት ለውጥን የሚሟገትለት የተቀናጀ አካል መፍጠር ነው። የአካባቢ ጥበቃ መብት ማስጠበቅ የመኖር ዋስትናን ማረጋገጥ ነው ሲሉ አቶ ነጋሽ ይናገራሉ።
የዘንድሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የአካባቢ ቀን የተከበረው ‹‹የሥነ ምህዳር ማገገም ለአገር ልማት›› በሚል በሀዋሳ ከተማ ነው።

በአካባቢ ጥበቃና በዱር ሕይወት ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማትን የሚያስተባብረው PHE ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በውይይት አክብሯል።
በዓሉን በውይይት ብቻ ማክበር ሳይሆን የተነሱ ሀሳቦችን ወደ መሬት በማውረድ ማን ምን መሥራት አለበት የሚለውን የምንለይበትና ወደተግባር የምንገባበት ነው የሚሉት ወ/ሮ ፍሬዘር ይሄይስ የ PHE ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ፓርትነርሺፕ ኤክስፐርት ናቸው።

ከግል፣ ከመንግሥት፣ ከሲቪክ ማኅበራት እና ከሚዲያ የተወጣጡ ባለሙያዎች መጫወት ያለባቸውን ሚና ለማወቅ የተዘጋጀ መድረክም እንደሆነ ገልጸዋል።
ለአካባቢ መጎዳት የሕዝብ ቁጥር መጨመር አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። በተለይ በድህነት ውስጥ ያለ ማሕበረሰብ ተፈጥሮን ለማውደም አማራጭ የለውም።በማሕበረሰብና በአካባቢ መስተጋብር ላይ ጥናት ያቀረቡት ከፕላን ኮሚሽን ተፈራ ደገፉ (ዶ/ር) ናቸው።

ችግሩ በታዳጊ አገራት ጎልቶ እንደሚታይ ይናገራሉ። ሕዝብና አካባቢ የተቆራኘ ነው። ሕዝብ ደግሞ በጣም እየበዛ ሲሄድ ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኘ ይሆናል። አገራችን በኢኮኖሚ ደካማ የሚባል ማህበረሰብ የሚባል በመሆኑ አካባቢን ይጠቀማል። የደን ሽፋን አሻሻልን ማለት አካባቢውን ማሕበረሰብ መጥቀም ይችላል ሲሉ ይናገራሉ።

የአየር ንብረትን ለመከላከል የ PHE ስብጥር ስልት መጠቀም አስፈላጊ ነው ሲሉ ፍሬዘር ይጠቅሳሉ።
የማህበራዊ ህይወትና አካባቢ በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ናቸው።ይህንን ችግር በመለየት ሁሉም አካል በጋራ በመሆን እንዴት መፍታት እንዳለባቸው የሚያመላክት መድረኮች በማካሄድ PHE ትልቅ ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ፍሬዘር ተናገረዋል።

ሕብረተሰቡ ከማሳው ጀምሮ ከተፋሰሱ ጋር አስታርቆ ይህን ትስስር ተገንዝቦ ከተሰራ የምግብ ዋስትናችንን ማስጠበቅ ይቻላል ብለዋል።
እንደዚህ አይነት ቀኖች ሲታሰቡ ማሕበረሰቡ መለስ ብሎ የት ጋር ነው ያለነው ብሎ እንዲያስብ እና ግንዛቤውን እንዲያሳድግ የPHE አላማ መሆኑን ወ/ሮ ፍሬዘር ጠቁመዋል።
ግጭቶች፣ የኮቪድ ወረርሺኝ እና ሌሎች የምናያቸው ችግሮች በመሉ በቀጥታ ከአካባቢ ጋር ግንኙነት ያላቸውና ችግር የሚፈጥሩ ናቸው።

በዕለቱ ከቀረቡት ጥናቶች ውስጥ ከዓለም አቀፍ በበይነ መረብ ገለጻ ያደረጉት በUNEP የዋና ዘርፍ ግሩፖች ሰብሳቢ ኢንግሪድ ሮስትድ የአካባቢ አስተዳደር እና ለአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያለውን አስተዋጽኦ በዝርዝር አስረድተዋል። በጥናታቸው ባለድርሻ አካላት ችግሮችን በመገንዘብና መርጦ በማውጣት መፍትሄዎች ላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በብዝኃ ሕይወትና ዘላቂ የሆነ የሰው ልጆች ደህንነት ያለውን ቁርኝት በጥልቅ ያስረዱት የ HOAREC ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ጆን ሞዪ ቬነስ ለመድረኩ ታዳሚዎች ለመወያያ መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦችን አቅርበዋል።
እንደነዚህ አይነት ዓለም አቀፍ በአላት ስናከብር ሁልጊዜ ለሕብረተሰቡ በምን መልኩ መድረስ እንዳለበት ለመገንዘብ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች በክልል የሚገኙ አመራሮችና የማሕበረሰብ ተወካዮች ሁሉም የየራሱን የቤት ሥራ እንዲሠራ ተመላክቷል ሲሉ ወ/ሮ ፍሬዘር ተናግረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 137 ሠኔ 12 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com