የእለት ዜና

ኢትዮጵያውያኖቹ በማጣሪያው ውድድር ድልን አስመዘገቡ

በቶኪዮ 2020 ሀገራችን በርካታ አትሌቶችን የምታሳትፍበት እና ተጠባቂው የአትሌቲክስ ውድድር ተጀምሯል::

ኢትዮጵያዊያኖቹ አትሌቶች ትናንት ሀሙስ ሀምሌ 22 ከለሊቱ 9:00 ጀምሮ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በተካሄደው በ3,000 እና 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ላይ ድልን አስመዝግበዋል።

በወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ጌትነት ዋለ፣ ለሜቻ ግርማ እና ታደሰ ታከለ ሲወዳደሩ ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በ8:09.83 በመግባት አንደኛ ሆኖ አልፏል።

ለሜቻ ግርማንም በመከተልጌትነት ዋለ በ8:12.55 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ማጣሪያውን አልፏል።

አትሌቶቹም የፊታችን ሰኞ ለሚደረገው የፍጻሜ ፍልምያ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል::

በተጨማሪም ሀብታቸው አለሙ ፣ ነፃነት ደስታ እና ወርቅውሀ ጌታቸው በሴቶች 800 ሜትር የማጣሪያ ውድድርን ያደረጉ ሲሆን ሀብታም አለሙ በ2:01.20 በመግባት ከምድቧ 2ኛ በመሆን ለነገው የግማሽ ፍፃሜ ውድድር የሚያበቃትን ሰዓት አምጥታለች::

በዛሬ እለትም ከሰዓታት በሗላ የሚካሄደው የሴቶች 5,000 ሜትር ማጣሪያ ሀገራችንን በፍፃሜው የሚውክሏትን አትሌቶች የሚለይ በመሆኑ በጉጉት ሲጠበቅ በመቀጠል የሚካሄደው የወንዶች 10,000 ሜትር ፍፃሜም ኢትዮጵያን ኦሊምፒኩ ከተጀመረ ወዲህ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ የምታስመዘግብበት እንድሚሆን ይታመናል::

አዲስ ማለዳ አትሌቶቹ ባስመዘገቡት ድል የተሰማትን ደስታ እየገለፀች በቀጣይም የሚከናወኑ ውድድሮችን ሀገራችን በድል እንድታጠናቅቅ መልካም ምኞቷን ማስተላለፍ ትወዳለች።

መረጃውን የአዲስ ማለዳው አብይ ወንድይፍራው ውድድሩ ከሚከናወንበት ከቶክዮ ኦሊምፒክ ስታዲየም ሆኖ አድርሶናል።

ድል ለአትሌቶቻችን!

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!