የእለት ዜና

ሚኒስትር ዴኤታው ከሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ከሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እየሰራችበት ስላለችው አለምአቀፍ የዲጂታል ትስስርና ስለፕሮጀክቱ እድገት እና የአተገባበሩ ቀጣይ ደረጃዎች ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ስለ ዲጂታይዜሽን አስፈላጊነት እና ክፍት እንዲሁም ተወዳዳሪ የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለአገሪቱ መፃኢ ዕድል ያለው አስተዋፆ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ዶ / ር ኢዮብ የኢትዮጵያ መንግስት ከአገር በቀል አጀንዳው አንዱ የሆነውን የሀገር ውስጥ ገበያን ለግሉ-ዘርፉ ውድድር መክፈት መሆኑን ገልፀው ይህም ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት እና ለተጠቃሚዎች የበለጠ አማራጭን ያመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ተሃድሶዎችም ለወደፊቱ የኢትዮጵያ የዲጂታል ጉዞ የለውጥ መሠረት እንደሚጥሉም አክለው ተናግረዋል፡፡

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ሁለተኛው የሞባይል ስልክ ኦፕሬተር ሆኖ መግባቱ በቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንትን ያስገኛል፤ እንዲሁም የተሻሻለ ውድድርን ወደ ገበያው ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል፣ ይህም በአገልግሎት ጥራት ፣ ሽፋን እና ፈጠራ መሻሻል ያስከትላል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፡፡

በተጨማሪም ለኢንዱስትሪው አገልግሎት ለመስጠት ኩባንያዎች ሲቋቋሙ እና አዲስ የቴክኖሎጂ ሥነ-ምህዳር ሲመጣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ሥራዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልፀዋ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አንዋር ሶሳም ለኢትዮጵያ መንግስት ሳፋሪኮም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማገልገል እድል ስለሰጠውና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያው ሥራ ለመጀመር በሚያደርገው ዝግጅት ላይ ጠንካራ ድጋፍ እያደረገለት ስለሚገኝ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!