የእለት ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሕልውና ዘመቻው ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ድጋፍ ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሕልውና ዘመቻው የሚውል ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ የዓይነት ድጋፍ ለአማራ ክልል አስረክቧል፡፡
ለሕልውና ዘመቻው የሚያደርገው ድጋፍ በአራት አቅጣጫ የተመራ መሆኑንም የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአፋር እና አማራ ክልል ድጋፉ በጎንደር እና ኮምቦልቻ በኩል እንዲደርስ እየተደረገ ነውም ተብሏል፡፡
በጎንደር በኩል ላለው የሕልውና ዘመቻ በግንባር የተደረገውን የከተማ አስተዳደሩን ድጋፍ ያስረከቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላት ናቸው፡፡
በዓይነት የተደረገው ድጋፍ ከከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶች እና ነዋሪዎች የተሰበሰበ መሆኑንም አቶ ዘላለም የገለጹ ሲሆን፣ 139 ሰንጋ፣ 1 ሺህ 809 በግና ፍየል፣ በኹለት መኪና የተጫነ ብስኩት፣ 121 ኩንታል ጤፍ እና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ናቸው ተብሏል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 143 ሐምሌ 24 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!