የእለት ዜና

የውጪ አገር ካምፓኒዎች የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች ለመከራየት ጥያቄ እንዳቀረቡ ተገለፀ

Views: 143

የውጪ አገር ካምፓኒዎች የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች ለመከራየት ጥያቄ እንዳቀረቡ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አሰታወቀ። የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች ለመከራየት ጥያቄ ያቀረቡት የቻይና እና የካናዳ ካምፓኒዎች እንደሆኑም ተነግሯል።
ባለፉት ዓምስት ዓመታት ኢትዮጵያ የቡና ስያሜዎቿን በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስጠበቅ ከ30 በላይ ከሚሆኑ አገራት ጋር የውል ስምምነት ማድረጓ ይታወቃል።አሁን የውል ስምምነቱ በመጠናቀቁ የተለያዩ አገራት የቡና ስያሜዎቹን ለመከራየት ፍላጎት እያሳዩ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አሳውቋል።
የሐረር፣ የይርጋጨፌና የሲዳሞ ቡና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘችባቸው የሀገራችን የቡና ስያሜዎች ሲሆኑ ከ 30 በላይ በሚሆኑ አገራት በንግድ ምልክትነት መመዝገባቸውና የስያሜዎቹ ህጋዊ መብት እንዲጠበቅ መደረጉን ባለስልጣኑ ገልጿል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ቡናውን ወደ ውጭ ስትልክ የውል ስምምነቱን ለፈረሙት ብቻ መሸጥ ሲኖርባት የውል ፈራሚዎች ጥምረቱ እንዳይጠናከር በሚያደርግ መልኩ ቡና መግዛት ለሚመጣ ሁሉ እየሸጠች ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ የአምራዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ኢትዮጵያ በራሷ እጅ ውሉን ማፍረሷን አሳውቋል።በዚህም ምክንያት አለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያን የቡና ስሞች ለመከራየት ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተነግሯል። ሁለቱ የቻይናና የካናዳ ኩባንያዎች የኢትዮጵያን የቡና ስያሜዎች በየአምስት አመቱ በሚታደስ ውል መሰረት ለመከራየት ጥያቄ ማቅረባቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።


ቅጽ 3 ቁጥር 143 ሐምሌ 24 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com