የእለት ዜና

የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የቁጫ ሠላም በር ምርጫ ክልል አሸናፊ ሆነ

የድምጽ መደመር ሒደቱ እንዲቆም ውሳኔ የተሰጠበት የቁጫ ሠላም በር ምርጫ ክልል ላይ፣ የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አሸናፊ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ክልሉ ከመነሻው ጀምሮ ቅሬታና አቤቱታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎቸ በመቅረባቸው ሊከሰቱ የሚችሉ ሥጋቶችን ለማስቀረት ሲል ውሳኔ ማሳለፉን ገልጿል።
የድምጽ መደመር ሒደቱ እንዲቆም እና ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ ሠነዶቹ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደረግላቸው ማድረጉን የተናገረው ቦርዱ፣ የድጋሜ ቆጠራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። ቦርዱ የመጀመሪያውን ዙር ምርጫ አካሂዶ በድምጽ ቆጠራ ወቅት ችግር የገጠማቸው ቦታዎች ላይ ሒደቱ ባለበት እንዲቆም መወሰኑ የሚታወስ ነው።
ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የተወዳደሩበት የቁጫ ምርጫ ክልል፣ የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አሸንፏል።
ለክልል ምክር ቤት ሦስት ወንበሮች 19 እጩዎች ቀርበው የነበረ ሲሆን፣ ሦስቱንም የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አሸንፏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 143 ሐምሌ 24 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!