የእለት ዜና

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ ጉዳዮች USG እና የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተወያዩ

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የተ.መ.ድ. የሰብዓዊ ጉዳዮች USG እና የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ሆነዉ በቅርቡ ከተሾሙት ማርቲን ግሪፊትስ ጋር ተገናኝተዉ በትግራይ ክልል ስላለዉ የጸጥታና የሰብአዊ እርዳታ ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡

ሚስተር ግሪፊትስ የተ.መ.ድ. የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ፍላጎቶች በሚያሟላ መልኩ መስራት እንደሚፈልግና ከሀገሪቷ ጋር ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰራም አስታዉቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ አሳሳቢ የሆኑትን ሰብአዊ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከUNOCHA ጋር ያለዉን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸውን ከፕሬዝደንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!