የእለት ዜና

“የዕዙ የሠራዊት አባላት የህውሓት ቡድንን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ይገኛሉ”፡- ሜ/ጀ መሰለ መሠረት

የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል መሰለ መሠረት የዕዙ የሠራዊት አባላት አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ግብዓተ መሬት ለማስገባት በአስተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡
ሜጀር ጀኔራል መሰለ ወደ ምዕራብ ዕዝ የተቀላቀሉትን መሰረታዊ ወታደሮች አቀባበል በተደረገላቸው ጊዜ እንደተናገሩት እንደ እባብ አፈር ልሶ የተነሳው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቢዳክርም የህልም ቅዠት ይሆንበታል፡፡
የዕዙ የሠራዊት አባላት ህግ በማስከበርና የህልውና ዘመቻ ወቅት የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን አከርካሪውን በመስበርና የቡድኑን ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስራ በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ዕዝ ነው ብለዋል፡፡
ዕዙን የተቀላቀሉ የሠራዊት አባላት በበኩላቸው የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው አሸባሪው ህወሓትን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!