የእለት ዜና

ገዳ ባንክ የመስራቾች ጉባኤ ማካሄዱ ተገለጸ

በ550 ሚሊዮን ገቢ በሆነ ብር እና በ1.3 ቢሊየን የተመዘገበ ካፒታል አክሲዮን የተመሠረተው ገዳ ባንክ የመስራቾች ጉባኤ ማካሄዱ ተገለጸ።
በገዳ ስርዓት የሚመራ እንደሆነ የተነገረለት የገዳ ባንክ፣ በኹሉም የሥራ መስክ ላይ የተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ ይሆናል ነው የተባለው።
በአጠቃላይ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እና ከ27 ሺሕ በላይ አባላት ያሉት ባንኩ፣ በመላው የአገሪቷ ክፍል ውስጥ በመንቀሳቀስ ለመሥራት አቅዷል።
በተለይም በልማት ምክንያት የካሳ ክፍያ ተከፍሏቸው ከቦታቸው የሚነሱ አርሶ አደሮችን ማዕከል በማድረግ ይሠራል ነው የተባለው።
አርሶ አደሮች ለዘመናት ያፈሩት ቤት እና ንብረት በልማት ምክንያት የካሳ ክፍያ ተከፍሏቸው እንዲነሱ ሲደረግ ራሳቸውን መልሰው እንዲያቋቁሙ የስልጠና እና ሌሎች ድጋፎች ስለማይደረግላቸው ወደ ከፋ ድህነት ውስጥ ይወድቃሉ።
ይህን ታሪክ ለመቀየር እሠራለሁ ያለው ገዳ ባንክ፣ እስካሁንም ባደረገው እንቅስቃሴ ከ8000 በላይ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ማግኘቱን እና እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ አክሲዮን የገዙ መኖራቸውን አቶ ዋሲሁን ሚጢ የባንኩ መስራች አስተባባሪ ኮሚቴ ተናግረዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!