የእለት ዜና

የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የደንብ ልብስ ለብሰው ከሚያጭበረብሩ አካላት ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የፌዴራል ፖሊስ አሳሰበ

የፖሊስ አባላት ሳይሆኑ “ፖሊስ ወይም የጸጥታ አካላት ነን” በማለት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ንጹሐን ዜጎች ስልክ በመደወል የዛቻ ወንጀል የሚፈፅሙና የሚያስፈራሩ ግለሰቦች እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ገልጿል። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የፌዴራል፣ የክልልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው፣ ሐሰተኛ መረጃ ይዘው፣ ሕገ-ወጥ ብርበራና የዝርፊያ ሙከራ የሚፈጽሙ እንዳሉ ከሕዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጨማሪ መረጃዎችንም እንዳሰባሰበ ነው ፖሊስ ያስታወቀው።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስም በማሳሰቢያው መሰል ድርጊት የተፈፀመባችሁ ግለሰቦች ወይም በቀጣይ ከሕግና አሠራር ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሲያጋጥም ለፖሊስ አፋጣኝ ጥቆማ እንዲያቀርቡ ተጠይቋል። ድርጊቱ ሕገ-ወጥ እንደሆነና በአሸባሪው ሕወሓት ጁንታ ቡድን ርዝራዦች ሊፈፀም እንደሚችልም ነው ፖሊስ ያሳሰበው። ተመሳሳይ ድርጊት ሲያጋጥም ወደ ተቋሙ የስልክ መስመሮች ፈጥኖ በመደወል ሕገ-ወጥ ግለሰቦችን ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ለሚደረገው ጥረት የበኩላቹን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com