የእለት ዜና

ምርጫ ቦርድ በምርጫ ጉዳይ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ወይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አገር ዐቀፍ ምርጫውን አስመልክቶ የመጀመሪያ ዙር መግለጫ ካወጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል። በውይይቱ አምስቱም የቦርድ አመራሮች፣ የቦርዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ኹሉም የቦርዱ የሥራ ክፍል ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብረቱካን ሚዴቅሳ ማኅበራቱ ለምርጫው ስኬታማነት የነበራቸውን አስተዋጽዖ ጉልህ እንደነበር ገልጸዋል።
የምርጫ ሒደትና ውጤትን ከሚሳያልጡ አካላት ውስጥ ሲቪል ማኅበራት ተጠቃሽ እንደሆኑና አገር ዐቀፍ ምርጫውን አስመልክቶም ያቀረቡት ቀዳሚ መግለጫ እንዲሁም በቀጣይም የሚያወጡት መግለጫ ለምርጫ ሒደት መሻሻል ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ሰብሳቢዋ ጠቁመዋል። ምርጫ በባህሪው በየጊዜ መሻሻል የሚጠይቅ ሒደት እንደሆነ የገለጹት ሰብሳቢዋ፣ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዜጎች ስለምርጫ የሚኖራቸውን መረዳት ከፍ ማድረግና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችም መሥራት ምርጫ ሲደርስ ብቻ ሊሆኑ እንደማይገባ ጠቁመዋል።
የሲቪል ማኅበራቱ አገር ዐቀፍ ምርጫው ላይ ስለታዘቡት አጠቃላይ ሁነት በውይይት መድረኩ አቅርበዋል። የምርጫ ቅስቀሳው ሰላማዊነት፣ ባለድርሻ አካላትና ፓለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርዱ ላይ ያሳደሩት ዕምነት፣ በቦርዱ የተሠሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣ የአካታችነት ሥራዎች፣ የተሰጡ ሥልጠናዎች እና ሕጎችን የማዘመን ሥራ በጥንካሬነት ከተጠቀሱት ውስጥ ሲገኙ፣ በአንጻሩ የታዛቢነት ባጆች በጊዜ ያለመድረስ፣ በምርጫ ክርክር ወቅት የምልክት ቋንቋን ያለመጠቀም እና ማኅበራቱ የሚፈለገውን ያህል በጀት መፍጠር ያለመቻላቸው ከተጠቀሱት ውስንነቶች ውስጥ ዋናዋናዎቹ ናቸው።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com