የእለት ዜና

ልማት ባንክ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር እንዳልተመለሰለት አስታወቀ

የኅብረት ሥራ ማኅበበር ከልማት ባንክ የተበደረውን ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ አለመመለሱ ተገለጸ።
ከተሰጣቸው ብድር በውላቸው መሠረት ባለፉት ኹለት የክፍያ ጊዜያት 166ቢሊዮን 518ሚሊዮን 823ሺሕ ብር የተመለሰ ሲሆን፣ በመክፍያ ጊዜው ያልመለሱ 11 ኅብረት ሥራ ማኅበራት 46ቢሊዮን 203ሚሊዮን 228ሺሕ ብር አልተመለሰም ሲል የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለአዲስ ማለዳ አረጋግጧል።

ባለፉት ስድስት ወራት ለግብርና እና ሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት የተፈቀደን 800 ሚሊዮን ብር ብድር ለ75 ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲሰራጭና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ክትትልና ድጋፍ መደረጉንም ተቋሙ አስታውቋል።
በ12 ክልሎች ለ86 ኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ 877ሚሊዮን 496ሺሕ 434 ብር ብድር ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ለ56 ኅብረት ስራ ማኅበራት ብር 366 ሚሊዮን 205ሺሕ 768 በባንኩ ተፈቅዶ ከዚህ ውስጥ 45 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ብር 345ሚሊዮን 902ሺሕ 132 መውሰድ መቻላቸው ተገልጿል።

ለ11 ኅብረት ሥራ ማኅበራት የተፈቀደውን 20 ሚሊዮን 303ሺሕ 636 ብር ኹለቱ በወለድ አልባ፣ ሰባቱ በትግራይ ክልል ባለው የጸጥታ ምክንያት፣ ኹለት ደግሞ የግብር ከፋይ ምዝገባ ባለሟሟላታቸው ብድሩን መውሰድ አልቻሉም።
በአጠቃላይ የብድር አቅርቦት የዕቅድ አፈጻጸሙም በጠቅላላው ከተፈቀደው አንጻር 43 በመቶ፣ ከ56 ኅብረት ሥራ ማኅበራት አንጻር 94 በመቶ ነው።

የብድር ጥያቄ ሰነድ ካቀረቡ 86 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ውስጥ ለ30ዎቹ ብድሩ ያልተፈቀደላቸው ሲሆን፣ ለዚህም የተሰጠው ምክንያት 25 ማኅበራት 352ሚሊዮን 250ሺሕ ብር ከፍተኛ የብድር ዕዳ ያለባቸው መሆኑ፣አንድ ማኅበር 2ሚሊዮን ብር የግብይት አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ መሆን፣ እንዲሁም አራት ማኅበራት በ 38ሚሊዮን ብር የኦዲት ሪፖርቶች ላይ ኪሳራ ላይ መሆናቸው ነው። በዚህም ምክንያት እነዚህ ማኅበራት ብድር መውሰድ እንደማይችሉ ልማት ባንክ አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የዋጋ ንረት ለመፍታት ፕሮጀክት በመቅረጽ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ 800 ሚሊዮን ብር መፍቀዱ ይታወሳል።
ለአገር ውስጥ ግብይት ፋይናንስ ብድር አቅርቦት በተደረገዉ ድጋፍ ለ 88 ኅብረት ሥራ ማኅበራት 800 ሚሊዮን ብር በማስፈቀድ እስካሁን በተደረገው ድጋፍ 51 ማኅበራት 341ሚሊዮን 381ሺሕ 832 ብር የብድር ፎርማሊቲዉን በማሟላት መውሰዳቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የብድር ጥያቄ ሰነዳቸው ተገምግሞ ለልማት ባንክ የተላከው የሦስት ኅብረት ሥራ ማኅበራት 77ሚሊዮን 700ሺሕ ብር መሆኑም ታውቋል። ሌሎች 34 ኅብረት ሥራ ማኅበራት ብድሩን ለማግኘት ከፍተኛ የብድር ዕዳ ያለባቸው እና አፈጻጸማቸውም ዝቅተኛ ሆኖ የተገኘ በመሆኑ ብድር መውሰድ እንደማይችሉ ልማት ባንክ አስታውቋል።

በበጀት ዓመቱ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ከዕቅድ በላይ 9 ቢሊዮን 959ሚሊዮን 228ሺሕ 490 ብር የኢንዱስትሪ ውጤቶች፣ የድጎማና የግብርና ምርቶች ግብይት ማከናወኑን አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተፈቀደው 500 ሚሊዮን ብር ለግብርና ምርቶች የግብይት ፋይናንስ ውስጥ 10 ሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 300 ሚሊዮን ብር ብድር ተፈቅዶላቸው 77ሺሕ ኩንታል ምርት በመግዛት ለሸማቹ ማሰራጨት እንደተቻለ ታውቋል። በግብይት ፋይናንስ አቅርቦት ሒደት በተደረገ ድጋፍ የተገኙ ውጤቶች በተመለከተ የግብይት ብድር የምርት የማሰባሰብ እና የማቅረብ አቅማቸው ያደገ የኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ የግብርና ምርት አቅርቦት ችግራቸውን መፍታት ችለዋል ነው የተባለው።

ለሸማቹ ሕብረተሰብ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ፣ በዝቅተኛ ወለድ በተፈቀድ ብድር ተጠቃሚ የሆኑ፣ የግብይት ድርሻቸው ያደገ የኅብረት ሥራ ማኅበራት መፈጠራቸውንም ተቋሙ ገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 144 ነሐሴ 1 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!