የእለት ዜና

ምርጫ ቦርድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተተኪ ዕጩዎችን እንዲያሳውቁ ዕድል መስጠቱን አስታወቀ

ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ተወዳዳሪ ሆነው መቀጠል ለማይችሉ ዕጩዎች ተተኪ የሚሆኑ ዕጩዎችን ለመቀየር ፓርቲዎች ካሳለፍነው ሐሙስ ማለትም ከነሐሴ 6 እስከ ቅዳሜ ነሐሴ 8/2013 ድረስ ማመልክት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጳጉሜ 1/2013 ምርጫ በሚያካሂድባቸው አካባቢዎች ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በዕጩነት አቅርበዋቸው ከዓቅም በላይ በሆነ ምክንያት ያቀረቧቸው ግለሰቦች በዕጩነት መቀጠል የማይችሉ ከሆነ፣ ፓርቲዎቹ ተተኪ ዕጩ ለማቅረብ እንዲችሉ ቦርዱ የመጨረሻ ዕድል ለመስጠት የሚያስችል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡በዚህም መሠረት ከነሐሴ 6/2013 ጀምሮ ባሉት ሦስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ለቦርዱ የፖለቲካ የሥራ ክፍል ማመልከት እንደሚቻል ቦርዱ አስታውቋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 145 ነሐሴ 8 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com