የእለት ዜና

ቴስላ የመኪና አምራች ድርጅት ላይ ክስ ተመሰረተ

ባለቤትነቱ የአሜሪካዊው ቢሊየነር ኤሎን መስክ በሆነው ቴስላ የመኪና አምራች ድርጅት ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡

በቴስላ የመኪና አምራች ድርጅት የተመረቱ መኪኖች ያለ ሹሬር በሚነዱበት ወቅት አደጋዎችን እያደረሱ መሆኑን ተከትሎ የአሜሪካው ብሔራዊ የመንገድ እና ትራፊክ ኤጀንሲ በመኪኖቹ ላይ ምርመራ ለማድረግ አስቤያለሁ ብሏል፡፡

ቴስላ እ.ኤ.አ  ከ2014 ጀምሮ አምርቶ ከሸጣቸው የመኪና ሞደሎቹ ውስጥ 750,000 የሚገመቱት መኪኖች ችግር እንዳለባቸው ኤጀንሲው ማረጋገጡን ተናግሯል ሲል ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ኤጀንሲው ከደረሱት 31 የሚደርሱ የአደጋ ሪፖርት ውስጥ 25 የሚሆኑት ያለ ሹፌር በመነዳታቸው እንደሆነ እና ከነዚህ ውስጥም 10 የሚደርሱት አደጋዎች ሞት ማስከተላቸውን አሳውቋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!