የእለት ዜና

ቦርዱ በሱማሌ ክልል የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ አስመልክቶ ያካሄደውን የምርመራ ሪፓርት አቀረበ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሱማሌ ክልል የተካሄደውን የመራጮች ምዝገባ አስመልክቶ በአጣሪ ባለሙያዎች ያካሄደውን ምርመራ ሪፓርት ለፓርቲዎች አቀረበ። ነሐሴ 11/2013 በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተካሄደውን የመራጮች ምዝግባ አስመልክቶ በባለሙያዎች አጣሪ ቡድን ማጣራት ማከናወኑ ተገልጿል።
በመድረኩም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ የቦርዱ ሁሉም አመራሮች መገኘታቸውም ታውቋል። በምርምራ ላይ ከተሠማሩት ዘጠኝ ቡድኖች ተወካዮች ቀርበው በየምርጫ ክልሎቹ ያደረጉትን ምርመራ ሒደት፣ ውጤት እና ለቦርዱ የሚያቀርቡትን የውሳኔ ሐሳብ አስረድተዋል።በምርመራ ሂደቱም በቀረቡት ቅሬታዎች ላይ ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ግለሰቦች ጋር ባደረጓቸው ቃለመጠይቆች፣ በመሥክ ጉብኝት፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ በሰበሰቧቸው መረጃዎች፣ ከፎቶና ከተንቀሳቃሽ ምስል እንዲሁም የቀረቡ የተለያዩ የሠነድ ማስረጃዎችን በመጠቀም ያጠናቀሩትን ሪፖርት አቅርበዋል።
የአጣሪ ቡድኑ ሪፖርት ከተሰማ በኋላ ቅሬታ ያቀረቡ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ሐሳብ እንዲሰጡ የተደረጉ ሲሆን፤ ፓርቲዎቹም ቅሬታዎቻቸውን እና ከቦርዱ የሚጠብቁትን የውሳኔ ዓይነት በተመለከተ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ቦርዱ ውሳኔዎቹን ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች በቅርቡ እንደሚያሳውቅ በምክትል ሰብሳቢው አማካይነት መገለፁን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 146 ነሐሴ 15 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com