የእለት ዜና

የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሰኔ 14/2013 በተካሄደው ምርጫ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላይ በታዛቢነት የተሳተፉ የሲቪክ ማኅበረስብ ድርጅቶች በምርጫ ወቅት የገጠማቸውን ችግር፣ የምርጫው አሳታፊነት፣ የምርጫውን ገለልተኝነት፣ የምርጫውን ተአማኒነት እና ኮቪድ 19 በምርጫው ላይ የፈጠረውን ተጽዕኖ አንስተው የልምድ ልውውጥ አድርገውል።
በምርጫው ታዛቢዎችን በማሰማራት እና የምርጫ አስፈጻሚዎችን በማስልጠን የተሳተፉ ሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች የልምድ ልውውጥ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥና የምክክር መድረክ ነው።
በሲቪክ ማኅበረሰቦቹ የልምድ ልውውጥ ላይ በምርጫው ውቅት የገጠሙ ችግሮች የተነሱ ሲሆን፣ የልምድ ልውውጡ ወደፊት ለሚደረጉ ምርጫዎች በተለይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደ ግብዓት እንደሚያገልግል ተገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 146 ነሐሴ 15 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com