የእለት ዜና

የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎችን ቅጣት በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መክፍል የሚቻልበትን አዲስ አሰራር ለመዘርጋት ስልጠና እየተሰጠ ነው

የትራፊክ ደንብ ተላላፊ አሽከርክሪዎች ቅጣትን በኢትዮ ቴሌኮም በኩል በሲስተም መክፍል የሚቻልበትን አዲስ አሰራር ለመዘርጋት ለትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው አሽከርካሪዎች የትራፊክ ቅጣት ክፍያውን ለመፈፀም እና የተያዘባቸውን መንጀ ፈቃድ ለመውሰድ የሚወስደድባቸው ምልልስ እና ጊዜ ለመቆጠብ በማሰብ አዲሱን አሰራር ለመዘርጋት ማሰቡን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ኤጀንሲው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ቴሌ ብርን በመጠቀም በሲስተም የቅጣታቸውን ክፍያ መፈፀም የሚያስችል አሰራር ለመጀመር ለኤጀንሲው የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች እና ለትራፊክ ፖሊሶች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጿል፡፡

ስልጠናው ኤጀንሲው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ተግባራዊ የሚያደርገው በሲስተም የሚፈፀመው ክፍያ ቴሌ ብርን በመጠቀም የትራፊክ ደንብ ተላላፊ ተቀጪዎች በተቀጡበት ቦታ ሆነው መክፈል የሚያስችል ሲስተም አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እና ኢትዮ ቴሌኮም በጋራ በመስጠት ላይ የሚገኘው ስልጠና ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በከተማዋ አዲሱን ሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ ለኤጀንሲው የትራፊክ ቁጥጥር ሰራተኞች ፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለተውጣጡ ከሁለት ሺ በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች እየተሰጠ መሆኑን ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!