የእለት ዜና

ኹለተኛው ዙር ምርጫ መስከረም 20/2014 እንዲካሄድ ተወሰነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14/2013 ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ኹለተኛው ዙረት ምርጫ መስከረም 20/2014 እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቀ። ድምጽ አሰጣጡ የሚከናወነው በሱማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ሲሆን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን እንደሚከናወን ቦርዱ አሳውቋል።
ቦርዱ ነሐሴ 13/2013 ምርጫ ባልተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አደርጓል። ኹሉም የቦርዱ አመራሮች የተገኙበትን የምክክር መድረክ በቦርዱ ዋና ሰብሣቢ ብርቱካን ሚደቅሳ አማካይነት ቦርዱ ሲሠራቸው የቆያቸው ሥራዎች ሪፓርት ለፓርቲዎች ማቅረቡን ጠቅሷል።
ቦርዱ በአጠቃላይ አገሪቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ከግንዛቤ አስገብቶ ከፓርቲዎቹ ጋር ለመምከር ማሰቡን ተሣታፊዎቹ አድንቀው፣ በአስተያየታቸውም፤ አገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ምርጫ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት የሰጡ ሲኖሩ፤ በአንጻሩ ደግሞ ሰኔ 14/2013 የተደረገውም ምርጫ የተደረገው በተመሳሳይ የጸጥታ ችግር በነበረበት ሁኔታ፣ አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አካባቢዎች ተለይተው እንደተካሄደ ጠቅሰው፣ አሁን የሚካሄደው ምርጫም እንደቀደመው ኹሉ የተሻለ ጸጥታ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ማካሄድ እንደሚቻል ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጠቁመዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 147 ነሐሴ 22 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!