የእለት ዜና

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በቤኒሻንጉል ለተገደሉበት ዕጩ ምትክ ማቅረቡን አሳወቀ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ(ቦዴፓ) አባል እና በክልሉ መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ለክልል ምክር ቤት ድርጅቱን ወክለው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አይናድስ ሞላ ደንበሩ በግልገል በለስ ከተማ ሐምሌ 13 /2013 ሞተው መገኘታቸውን ፓርቲው ማሳወቁ ይታወሳል።
ፓርቲው በተሻሻለው የምርጫ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች ስነምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 40 (1) መሠረት ወደፊት በዞኑ ለሚካሄደው ምርጫ ምትክ ዕጩ አቅርቦ ለማስመዝገብ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ገልጿል። ቦርዱ ተተኪ ዕጩ እንዲያስመዘግብ ለፓርቲው በሰጠው ፈቃድ መሠረት በሞቱት ዕጩ ተወዳዳሪ አይናድስ ሞላ ደንበሩ ምትክ መለሰ ኤርሚያስ ተራኖ አቅርቦ እንዲተኩ ማድረጉን ቦዴፓ አስታውቋል።
ፓርቲው ከዚህ በፊት በክልሉ አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ እንደተገደሉበት መግለጹ የሚታወስ ነው። በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ እንዲወዳደሩ በዕጩነት አቅርበዋቸው ከተደገሉባቸው መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ)፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) እና እናት ፓርቲ ይገኙበታል።


ቅጽ 3 ቁጥር 147 ነሐሴ 22 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!