የእለት ዜና

49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ወደ ኮምቦልቻ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ዋለ

49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ወደ ኮምቦልቻ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የጽ/ቤቱ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሰይድ ለአሚኮ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪው ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር መዋሉም ታውቋል።

ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮማንደር አሊ ጠይቀዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!