የእለት ዜና

ባንኮች የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 ከፍ እንዲል ተደረገ

ባንኮች የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 ከፍ እንዲል መደረጉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገለጸ፡፡

ባንኮች ለአጭር ጊዜ የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመፍታት ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሚበደሩበት ዓመታዊ ወለድ ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 16 ከፍ እንዲል ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምን በተመለከተም በባንኮች በኩል በሚገኝ የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀም ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የባንኮች መጠባበቂያ እና የብሄራዊ ባንክ ማበደሪያ ወለድ ምጣኔን በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫው በፈርጆቹ አቆጣጠር ከመስከረም 1/ 2021 ጀምሮ ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንዲያስቀምጡ የሚገደዱት የመጠባበቂያ መጠን ከነበረበት 5 በመቶ ወደ 10 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑን ከኢትዮጲያ ፕረስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!