የእለት ዜና

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለ 37 ወለል ዋና መሥሪያ ቤቱን አስመረቀ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለ 37 ወለል የያዘ ዋና መስሪያ ቤቱን ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 29/2013 አስመርቋል።
ዋና መስሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ በራስ አበበ አረጋይ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት ፊት ለፊት የተገነባ ሲሆን፡ ከሚያዚያ 15/2013 ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የንብ ኢንተርሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት ገነነ ሩጋ አሳውቀዋል።
ህንጻው በአንድ ጊዜ 500 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ ከመሆኑም ባሻገር የህጻናት ማቆያ ማዕከል፤ ቤተ መፅሐፍት፤ የሰዉነት ማጎልመሻ ማዕከል፤ ክሊኒክና የሰራተኞች መመገቢያ አዳራሽ አካቶ የያዘ ነው ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ዘመናዊ ህንጻው ለሰውና ዕቃ ማመላለሻነት የሚያገለግሉ ስድስት እሳንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን፤ በማንኛውም ሰዓት ለሚያጋጥም የመብራት መቆራረጥን ለማስቀረት የሚረዱ ጀኔሬተሮች እንዳሉትም ነው ፕሬዝዳንቱ የጠቆሙት።
በንብ ቀፎ አምሳል የባንኩን ብራንድ ተመርኩዞ ህንፃው የተገነባ ሲሆን፣ በአገራችን ካሉት ህንጻዎች በተለየ ሁኔታ አገራዊና ባህላዊ እሴትን መግለጹ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ነው ፕሬዝዳንቱ የገለጹት።
ባንኩ በአጠቃላይ ከ7ሺህ 400 በላይ ሰራተኞችን ያቀፈ ከመሆኑም ባሻገር፣ የቅርንጫፍ አድማሱን በማስፋት በመላው የአገሪቱ ክፍል ከ380 በላይ የሚሆኑ ቅርንጫፎችን በመክፈት ከ1.7 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ደንበኞች ብቁ የሆኑ ሰራተኞች አገልግሎት አየሰጡ ይገኛል ነው የተባው።


ቅጽ 3 ቁጥር 148 ነሐሴ 29 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!