የእለት ዜና

ሳፋሪኮም ወደ ሥራ መግባት የሚያስችለውን እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ

ኢትዮጵያ የግል ቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ኢተዮጵያ ስራውን ለማስጀመር የሚያስፈልጉትን የተለያዩ ግብዐቶችን የማሟላት ስራ በመከወን ላይ መሆኑን አስታወቀ።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት አጋማሽ ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ሰራ ለመግባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የሣፋሪኮም ዋና ስራ አስፈጻሙ ፒተር እንዴግዋ የተናገሩ ሲሆን፣ ለዚህም ይረዳው ዘንድ የቴክኖሎጂ ግብዐቶችን በመሟላት ላይ እንደሆነም ገለጸዋል።
ሳፋሪኮም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በኢትዮጵያ የ8.5 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ እና የቴሌኮም አግልግሎቱ የተሻለ ለማድረ እንደሚሰራም ተገልጿል።

ዋና ስራ አስፈጻማ ተቋማቸው በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ በመቻሉ ትልቅ ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸው፣ ለዚህ ጉዞ መሳካት ትልቅ ትብብር ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድርጅቱ ኢትዮጵያ የግል ቴሌኮም አቅራቢ ድረጅት ለመሆን በይፋ እንቅስቃሴ መጀመሩን ባስታወቀበት መርሀ ግብር ላይ ተቋሙን የሚመሩ አመራሮችን አስተዋውቋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አግልግሎት መስጠት ሲጀምር ኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሁለቱንም ተቋማት ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ያስታወቀ ሲሆን፣ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አንዋር ሶሳ አስታውቀዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስከሚቀጥለው ሰኔ ወር ድረስ 1000 በፈጠራ እና በዲጂታል ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን ለመቅጠር እቅድ አለው። ከዚህም በተጨማሪም ተቋሙ discover graduate management program በሚል መንገድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት 450 ተመራቂዎችን በመምረጥ በአመራርነት ላይ ያተኮረ ስልጠና እንደሚሰጥም አስታውቋል።

በሚቀጥለው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ላይ ወደስራ የሚገባው የግል የቴሌኮም ቅራቢ ድርጅቱ በሚቀጥሉት ዓመታት ላይ የራሱን መሰረተ ልማቶች ለማለማት አቅዷል።

በተጨማሪም ከውጭ ለሚመጡ የቴሌኮም አቅራቢ ድረጅቶች ዝግ የሆነው ገንዘብን በሞባይል የማስተላለፍ እና የመቀበል አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችለውን እንቅስቃሴ መጀመሩ የታወቀ ሲሆን፣ ለዚህም ይረዳ ዠንድ ከመንግስት ጋር ውጤታማ የሚባል ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል።

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ላይ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም ዓቀፍ ጨረታ ላይ በመሳተፍ አሸናፊ መሆን የቻላ ዓለም ዓቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ የተሰኘው ተቋም ሲሆን፣ በጥምረቱ ውስጥም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን እና ሲዲሲ ያካተተ ነው።

ቴሌኮም አቅራቢ ተቋሙ ወደስራ ሲገባ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግርን ለማመምጣትና የዜጎችን ዕይወጥ ለመለወጥ እንደሚሰራም ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን እንቅስቃሴ ማሰጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አሰፈጻሚ ፒተር እንዴግዋ አስታውቀዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 148 ነሐሴ 29 2013

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!