የእለት ዜና

በመዲናዋ 51 ህገ-ወጥ እርድ የፈፀሙ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡-የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

Views: 85

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ በአራት ክፍለ ከተሞች ውስጥ 51 ህገ-ወጥ እርድ የፈፀሙ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቀጣይም ህገ-ወጥ እርድ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ተለይተው እርምጃ መወሰዱ እንደሚቀጥል ቢሮው ገልጿል፡፡

በከተማ ደረጃ ገበያን ለማረጋጋት የተሰማራው ግብረ-ሀይል በአራት ክፍለ ከተሞች ማለትም በቦሌ፤ በንፍስ ስልክ፤ በኮለፌ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ህገ-ወጥ እርድ የሚከናወንባቸው ቦታዎችን ለይቶ ባደረገው ክትትል 51 ህገ-ወጥ እርድ ተይዞ በግብረ-ሃይሉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

በተጨማሪም 229 በግና ፍየሎች በህገ-ወጥ መንገድ ለማረድ ተዘጋጅተውቄነበሩ አካላት በግብረ-ሃይሉ ባደረገው ክትትል መያዛቸውም ቢሮው ገልጿል፡፡

የንግድ ቢሮ ም/ሃላፍ የሆኑት መስፍን አሰፋ ይህንኑ አስመልክተው ባደረጉት ገለጻ፤ በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር የተሳተፉ ነጋዴዎችና ተቋማት እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት መቀጣታቸውን አስረድተዋል።

ቅጣቱም በከተማ ግብርና እና በድንብ ማስከበር ቢሮ በኩል እንዲፈጸም ከመደረጉ በተጨማሪ ሁለት ነጋዴዎች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እያላቸው በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር በመሳተፋቸው ንግድ ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ መደረጉንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ስራ ስኬት ህብረተሰቡ ባደረገው የነቃ ተሳትፎ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ መጪውን የአዲስ ዓመት በዓል ህብረተሰቡ በሰላም እንዲያሳልፍ ግብረ-ሀይሉ ገበያን የማረጋጋት ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com