የእለት ዜና

የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ከመጠለያ ጣቢያ የወጡ ስደተኞች እንዳሉ ገለጸ

Views: 38

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ተሰደው በሱዳን መጠለያ ጣቢያዎች የሚኖሩ ስደተኞች ከቅርብ ወራት ወዲህ ቁጥራቸው መቀነሱን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ የስደተኞች መታወቂያ ይዘው ከመጠለያ ጣቢያዎች በመውጣት በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ሲሳተፉ የተገኙ ታጣቂዎች አሉ መባሉን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፣ የተመዘገቡት ስደተኞች ኹሉ በመጠለያ ጣቢያው መኖራቸውንና አለመኖራቸውን የማጣራት ሥራ ማከናወኑን አስታውቋል።
ከመጠለያ ጣቢያዎች የወጡት ስደተኞች እንዳሉ የገለጸው ኮሚሽኑ፣ ነገር ግን ስደተኞቹ የት እንዳሉ ለማረጋገጥ አልቻልኩም ሲል አሳውቋል።
በተጨማሪም ከመጠለያ ጣቢያዎች ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱም ይሁን ወደ ትጥቅ ትግል የተቀላቀሉ ካሉ ዳግም ወደ መጠለያ ጣቢያ መመለስ እንደማይችሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።


ቅጽ 3 ቁጥር 149 መስከረም 1 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com