የእለት ዜና

በጎንደር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ጥይት ተያዘ

በጎንደር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ7 ሺህ በላይ የክላሽና የብሬን ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ።

በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በአንድ አዘዋዋሪ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 4 ሺህ 9 መቶ 78 የክላሸና 2 ሺ 7 መቶ 90 የብሬን ጥይት ተይዟል፡፡

እንደ ኢብኮ ዘገባ ጥይቶቹን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለው ብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከአማራ ክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር ነው።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com