የእለት ዜና

አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ድጋፍ አደረገ

አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ በኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በኮምቦልቻ ከተማ በመገኘት ደጋፋን በሃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም አትሌት ሃይሌ አበርክቷል።
ለተፈናቃዮቹ የተደረገው ድጋፍም 500 ኩንታል ዱቄት እና 2 ሺህ 500 ሊትር ዘይት ነው።

በተጨማሪም አትሌቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቡድኑ በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል።

በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድን አትሌት ሻለቃ ሃይለገብረ ስላሴ በአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን በዳስ ለሚማሩ ህጻናት ያስገነባውን ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ቤት ማውደሙ ይታወቃል።

አትሌቱ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ በተፈጸመው ድርጊት እጅግ ማዘኑን የገለጸ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን ማውደም በጦር ወንጀለኝነት መታየት እንዳለበትም ጠይቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!