የእለት ዜና

ከሳዑዲ አረቢያ 426 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 158 ህጻናትን ጨምሮ 426 ዜጎቻችን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!