የእለት ዜና

በሁሉም መስጊዶች ከመስከረም 7 እስከ መስከረም 25 ድረስ የሚቆይ የፀሎትና የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የተፈናቀሉና ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ በሁሉም መስጊዶች ከመስከረም 7 እስከ መስከረም 25 ድረስ የሚቆይ የፀሎትና የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው እለት በከተማዋ ከሚገኙ የመስጂድ ኢማሞች ጋር ውይይት አድርጓል።

በውይይቱም በጦርነት እና በሀገራችን በሚከሰቱ በተለያዩ ቀውሶች ህመማቸው የበዛ እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ለመርዳት ከመስከረም 7 እስከ መስከረም 25 ድረስ የሚቆይ የፀሎትና የድጋፍ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው የፀሎትና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ላይ ህዝበ ሙስሊሙ ሀላፊነቱን እንዲወጣም መልዕክት ተላልፏል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!