የእለት ዜና

በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 5 ሺህ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ከተማ ጨንገሬ ሶኪሌ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሜታ በሚባል ቦታ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 5 ሺህ ጥይቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አየለ አብደታ በተባለ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኙት 5 ሺህ የክላሽ ጥይቶች በህገወጥ መንገድ በከብቶች መኖ ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የወረዳው ፖሊስ ገልጿል፡፡

ጥይቶቹ ለሽብርተኞች ሊሰጡ እንደነበር የኤጄሬ ፖሊስ አዛዥ ሳጅን ሃይሉ ለቺሳ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ ሰላሙን ለማደፍረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላትን በመታገል ለህግ እንዲቀርቡ ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲሰራ ፖሊስ ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!