የእለት ዜና

ነገ አርብ ሁሉም ዜጋ የሚሳተፍበት የዘመቻ ጥሪ እንደሚካሄድ ተገለፀ

ነገ አርብ መስከረም 07 ቀን 2014 ከቀኑ 7፡07 ላይ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት በሚል እየተካሄደ ላለው ዘመቻ ሁሉም ዜጋ አጋርነቱን እንዲገልጽ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በእለቱ ሁሉም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የማህበራዊ መገናኛ ጉጻቸውን ፕሮፋይል በዚህ ፎቶ በመቀየር የዘመቻው አጋር መሆናቸውን እንዲገልጹ የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ንቅንቄ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢቢሲ ገልጿል፡፡

ነገ አርብ መስከረም 7 ቀን 7 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ላይ ሁሉም ዜጋ ይህን ጥሪ ተቀብሎ እንዲተገብር እና አጋርነቱን እንዲያሳይ ተጠይቋል፡፡

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!