የእለት ዜና

ለአሸባሪዎች ድጋፍ በማድረግ የተጠረጠሩ 15 ወንጀለኞች መከሰሳቸው ተገለጸ

በሐረሪ ክልል በሽብርተኝነት ለተፈረጀው ህወሓት እና ሸኔ ድጋፍ በማድረግ ወንጀል በተጠረጠሩ 15 ግለሰቦች ላይ ክስ መመሥረቱን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና ዐቃቤ ሕግ አዩብ አሕመድ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁትን ህወሓት እና ሸኔን በክልሉ የሚደግፉ ግለሰቦችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሕብረተሰቡ እና ጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል።
በዚህም በክልሉ “ለአሸባሪዎቹ” የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርጉ እና ለጥፋት የሚያነሳሱ ግለሰቦች እና ድርጅቶችን በመቆጣጠር የምርመራ ጉዳያቸው በሕግ እንዲታይ ክስ የመመሥረት ሥራ እየተካሄደ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
አሁን ላይ ሽብርተኛ ተብለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈረጁ ቡድኖችን በመደገፍ እና የሽብር ወንጀል በመፈጸም በተጠረጠሩ 15 ወንጀለኞች ላይ ክስ መመሥረቱን ነው አዩብ ያስታወቁት። በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው ተጣርቶ ከወንጀሉ ነጻ ሆነው የተለቀቁ ግለሰቦች እንዳሉም አያይዘው ጠቅሰዋል። እንዲሁም፣ ሰባት ድርጅቶች ታሽገው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመው። ባለንብረቶቹ ለጊዜው ቢሰወሩም 11 ተሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቅሰዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!