የእለት ዜና

ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር በታይም መጽሄት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ መንክር ታይም መጽሄት በአለም ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ካላቸው 100 ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።

ታይም መጽሔት በትምህርት ፣ በሳይንስ ፣ በኢኮኖሚክስ በሌሎች ዘርፎች ጨምሮ በ2021 በዓለም ላይ እጅግ ተጽእኖ ፈጣሪ ያላቸዉን የ100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ሰባት አፍሪካውያንን አካቷል፡፡

ከዚህም ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጲያዊቷ ሥራ ፈጣሪ እና የምግብ ፖሊሲ ባለሙያ ሳራ መንክር ተካታለች፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳራ በግብርና ነክ ጉዳዮች ላይ በመላው አለም ያለውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት የሚያሰችል ‘ግሮ ኢንተለጀንስ’ የተሰኘ ድርጅት በማቋቋም ትመራለች፡፡

ድርጅቱ አርሶ አደሮች እና መንግስታት በግብርናዉ ዘርፍ የተሻለ ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ የሚያግዝ ሲሆን በግብርና እና በከባቢ አየር ስጋት ዙሪያ በአለማችን በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ የመረጃ ተንታኝ ተቋማት መካከል አንዱ ነው።

በዝርዝሩ ዉስጥ ናይጄሪያዊቷ የዓለም ንግድ ድርጅት ኃላፊ ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ፣ የአፍሪካ ህብረት የኮቪድ ምላሽ የሚመሩት የካሜሮን ዜግነት ያላቸዉ ዶ/ር ጆን ኒንጋሶንግ እና የኬንያ የአካባቢ መብት ተሟጋች ፊሊስ ኦሚዶ መካታቸው ታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!