የእለት ዜና

የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ የሚኒስሮች ኮሚቴ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እያደረገ ነው

የብሄራዊ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አስተባባሪ የሚኒስሮች ኮሚቴ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር እና ከተባበሩት መንግስታትና ሌሎች አለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ ምክክር እያደረገ ይገኛል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ የፌደራል እና የክልሎቹ መንግስታት የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

አጋሮች ሰብዓዊ ድጋፍ እያስተባበሩ እና ስርጭቱን እየመሩ ባሉባቸው አካባቢዎች በትኩረት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት በተጠናከረ መልኩ ማካሄድ እንዳለባቸው ተገልጿል።

የሰብዓዊ አጋር ድርጅቶቹ ሃላፊዎች የበርካታ ዜጎች ሕይወት አደጋ ላይ መሆኑን እንደተገነዘቡና በቁርጠኝነት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!