የእለት ዜና

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች ምርጫ ካርድ እያወጡ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የሐረሪ ክልል ተወላጆች በተዘጋጀላቸው የምርጫ ጣቢያ የምርጫ ካርድ እየወሰዱ መሆኑን የሐረሪ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የክልሉ ተወላጆች በተዘጋጀላቸው ምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርድ እየወሰዱ ነው ያለው የክልሉ መንግሥት፣ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የሐረሪ ክልል ተወላጆች መስከረም 20/2014 ለሚካሄደው ምርጫ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ተናግሯል።
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ካርድ በመውሰድ ዲሞክራሲዊ መብታቸው ለመጠቀምና የሚበጃቸውን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጻል። በሐረሪ ክልል የሚገኘው ሕዝብና ከክልሉ ውጪ የሚኖረው የክልሉ ተወላጅ በቀሩት ቀናት የምርጫ ካርዱን በመውሰድ በምርጫው ላይ መሳተፍ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳዳር በተለያዩ አካባቢዎች ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች የተቋቋሙ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ለክልሉ ተወላጆች ምርጫ ጣቢያ እንዲቋቋም የተወሰነው የክልሉ መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!