የእለት ዜና

ለብዙኃን መገናኛ ቀደም ሲል የተሰጠው ባጅ ለኹለተኛው ዙር ምርጫ ያገለግላል ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አጠቃላይ ምርጫን መዘገብ ለሚፈልጉ ለአገር ውስጥና ለውጭ የብዙኃን መገናኛ አካላት እና ጋዜጠኞች በተለያየ ጊዜ የፈቃድ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጥሪ በማድረግ መዘገብ የሚያስችላቸውን ልዩ የዘገባ ባጅ መስጠቱ ይታወቃል። የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሰኔ 14/2013 በተካሄደባቸው አካባቢዎች ከቦርዱ ባጅ የተሰጣቸው ጋዜጠኞች የምርጫውን ሒደት በቅርብ እርቀት እንዲከታተሉ ማስቻሉ የሚታወስ ነው።
ልዩ ባጅ የወሰዱ የአገር ውስጥ የብዙኃን መገናኛ አካላት እና ጋዜጠኞች ቦርዱ በቀጣይ መስከረም 20/2014 ምርጫ ባልተደረገባቸው አካባቢዎችና የድጋሜ ምርጫ እንዲሁም የሕዝበ ውሣኔ የሚያካሂድባቸው አካባቢዎች የሚኖረውን የምርጫ ሒደት ለመዘገብ ቀደም ሲል ቦርዱ የሰጣቸውን ባጅ እንዲጠቀሙ ሲል ቦርዱ አሳስቧል። የኹለተኛው ዙር ምርጫ በሱማሌ እና በሐረሪ ክልል ሙሉ በሙሉ የሚደረግ ሲሆን፣ ከመጀመሪው ዙር ምርጫ ያልተካተተው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ይገኝበታል።v


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!