የእለት ዜና

ምርጫ ቦርድ ለኹተኛው ዙር ምርጫ የአየር ስዓት ድልድል አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር መስከረም 20/2014 በሚደረገው ምርጫ ላይ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚውል የነጻ አየር ሰዓት መደልደሉን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 28/013 ከኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛ ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በመጪው መስከረም 20/2014 ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል ዕጩዎች የሚውለውን የነጻ አየር ሰዓት ድልድል አካሂዷል። የአየር ሰዓት ድልድሉ መመሪያውን መሠረት አድርጎ፤ በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ለሚወዳደሩ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 106 የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች የቀረበ ሲሆን፣ ይህውም በሦስት ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በአራት ቴሌቪዥንና በኹለት ጋዜጦች ላይ የተደለደለ ነው ተብላል።
በድልድሉ በቴሌቪዥን 39 ሰዓታት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሲቀርብ፣ ለግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ደግሞ 26 ሰዓታት ከግማሽ ሰዓት ቀርቧል። በሬዲዮ 32 ሰዓታት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሲቀርብ፣ ለግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ደግሞ 26 ሰዓታት ከግማሽ ሰዓት ቀርቧል። በጋዜጦችም እንዲሁ በአጠቃላይ 45 ዐምድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርቧል። የነጻ የአየር ሰዓቱ ከጷግሜ 2/2013 ጀምሮ እስከ መስከረም 14/2014 የሚቆይ ነው።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!