የእለት ዜና

የኢትዮጵያ እና የኬኒያ የወደብ ላይ ግብይት ለማሳለጥ የጋራ ማዕከል እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ሞያሌ ወደብ ላይ በኬኒያ እና በኢትዮጵያ ድንበር መካከል በሚደረገው ግብይት የምንዛሬ ልዩነት በመኖሩ ምክንያት በዶላር መገበያየት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም የጋራ ድንበር አገልግሎት ማዕከል መጀመር አለበት ተብሏል።
የኬንያ አጓጓዦች ማኅበር ጸኃፊ ሜርሲ ኢሪሪ መስከረም 15 ቀን የኬንያ የንግድ ልዑካን ከኢትዮጵያ አቻዎች ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተናሩት፣ “የኬንያ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ችግር ላይ ናቸው፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ባንኮች የኬንያ ሽልንግን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው” ብለዋል።

የኹለቱ አገራት የጉምሩክ ኮሚሽነሮች በሞያሌ አንድ ማቆሚያ የድንበር ግብይት ላይ የጉምሩክ የሥራ ማኑዋሎችን አሠራር ተፈራርመዋል። የአንድ – አለቅ የድንበር አገልግሎት ማዕከል የድንበር ነክ ጉዳዮችን የሚቆጣጠሩ የመንግሥት ተቋማትና ሠራተኞች የተቀናጀ የድንበር አሥተዳደር ሥራዎችን በተሳካ መልኩ መተግበር እንዲችሉ የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም ነጋዴዎች፣ የጭነት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም አጓጓዦችና ሌሎች መንገደኞች ድንበር አቋርጠው ለመሻገር የሚያልፉባቸውን ሒደቶችን ቀላል፣ ፈጣን እና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ በማድረግ የድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎችን የተቀላጠፉ እንደሚያደርግም ታምኖበታል።
ኢትዮጵያ የሞያሌው ሥምምነት ከተሳካ በኋላ ተመሳሳይ የድንበር አገልግሎት ማዕከሎችን ከሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከጅቡቲ ጋር ለማቋቋም አቅዳለች።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 90 በመቶ የሚሆነው የውጭ ንግዷን በጅቡቲ በኩል የምታካሄድ ሲሆን፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ፣ ሶማሊላንድ፣ ሱዳን እና ኤርትራ የወደብ መዳረሻዎች በኩል የውጭ ንግዷን ማካሄድ ብትችል በጅቡቲ መስመር ያለውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል ተብሏል።
ማዕከሉ ሥራ ቢጀምርም፣ ባንኮች፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ፣ ኢሚግሬሽን፣ ትራንሥፖርት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያ በኩል ክፍት እንደሆኑ የኬንያ ልዑካን ተናግረዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ካቤታ “እኛ የጉምሩክ ፕሮቶኮል አዘጋጅተናል። የኢትዮጵያ መንግሥት አስቀድሞ፤ ለኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስገብቷል። በኢትዮጵያ በኩል እያንዳንዱን ዝግጅት አጠናቀን፤ ከኤርትራ በኩል ምላሾችን በመጠባበቅ ላይ ነን” ሲሉ ተናግረዋል።

አፍሪኤግዚም ባንክ ለንግድ ባንኮች የ 500 ሚሊዮን ዶላር አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑም በእለቱ ተገልጿል።

የአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ በባንኩ የንግድ ማመቻቸት መርሃ ግብር አማካይነት የአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት በወደቁ ወለዶች ላይ ያጋጠሙትን ተጽዕኖዎች ለመቋቋም ዓለም ዐቀፍ ባንኮች ለእነሱ ብድር እንደሚሰጡ እያሳየ ነው።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ እንደገለፁት፣ “ተደጋጋሚውን የምንዛሬ እጥረትን የሚያቃልል እና በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ንግድ ለማሳደግ ጠቃሚ ነው” ብለዋል።

በባንኮቹ መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ መካከለኛነት ለማስተዳደር በማዕከላዊ ባንክ በተዘጋጀው መመሪያ መሠረት፣ ባንኮቹ ከባለሀብቱ ብድር ያገኛሉ። ከአንድ ዓመት በፊት የተዘጋጀው መመሪያው የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ከዓለም ዐቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እንዲበደሩ ይፈቅዳል።


ቅጽ 3 ቁጥር 150 መስከረም 8 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!