የእለት ዜና

21 ሆስፒታሎች በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጉዳት እንደረሰባቸው ተገለፀ

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አሸባሪ በተባለው ህወሓት ተይዘው በነበሩ የአማራ እና የአፋር ክሎች አካባቢዎች በሚገኙ 21 ሆስፒታሎች፣ 287 የጤና ጣቢያዎች እና ከአንድ ሺህ አንድ መቶ በላይ የጤና ኬላዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የጤና ሚኒስቴር በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በአማራ ክልል በሚገኙ አምስት ዞኖች ውስጥ ባሉ 20 ሆስፒታሎች፣ 277 የጤና ጣቢያዎች ከአንድ ሺህ በላይ የጤና ኬላዎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም በተመሳሳይ በአፋር ክልል በሚገኝ አንድ ዞን ውስጥ 1 ሆስፒታል፣ 10 የጤና ጣቢያዎች፣ 38 የጤና ኬላዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡

ጉዳቶቹ በጤና ተቋማት ብቻ ሳይሆን በተቋማቱ በስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ መሆኑን በመግለፅ ከስራ ቦታቸው እንዲፈናቀሉ ቡድኑ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፁ አንቡላንሶች ጉዳት እንደደረሰባቸው ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል ሲል ብስራት ራዲዮ ዘግቧል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com