የእለት ዜና

ከ101 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ቁሳቁሶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ተይዘዋል

ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም ከ05/13/2013 እስከ 06/01/2014 ድረስ ከ101ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፤ የገቢ ኮንትሮባንድ 99ሚሊየን 494ሺህ 237 ብር ፤ ወጪ ደግሞ 2ሚሊየን 345ሺህ 048ብር በድምሩ የ101ሚሊየን 839ሺ 285ብር ግምት አላቸው ተብሏል፡፡

ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የወርቅ ማውጫ ማሽን፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድሀኒትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ዕቃዎች ውስጥ በድምሩ 80ሚሊየን 322ሺህ 616 ብር የሚሆነው በአ/አ ኤርፖርት ቅ/ጽ/ቤት በገቢ እና በወጪ የተያዘ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የዋጋ ግምታቸው 50ሚሊየን 260ሺህ 216 ብር የሆኑት ኤሌክትሮኒክሶች እንዲሁም የዋጋ ግምታቸው 27 ሚሊየን 606ሺህ 384ብር የሆኑት ደግሞ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች መሆናቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

error: Content is protected !!