የእለት ዜና

በሱማሌ ክልል ከሚወዳደሩ 4 ፓርቲዎች ሶስቱ አንሳተፍም ማለታቸው በምርጫ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡-የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 በሚካሄደው 2ተኛ ዙር ምርጫ በሶስት ክልሎች እንደሚካሄድ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው መግለጫ ዝርዝሩን ይፋ አድርጓል።

በመግለጫው ላይ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህዝብ በምርጫው እንደሚሳተፍበት የገለጹት የቦርዱ የኮዩኒኬሽን አማካሪ ሶልያና ሽመልስ፤ ምርጫውን ለማከናወን ቦርዱ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

በሶማሌ ክልል ሊወዳደሩ ከነበሩ አራት ፓርቲዎች 3ቱ አንወዳደርም ቢሉም በምርጫ ሂደቱ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ቦርዱ አሳውቋል።

ከነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ውጭ በደብዳቤ እንደማይሳተፍ ያሳወቀ የለም ያለው ቦርዱ፣ ፓርቲዎቹ ተሳተፉም አልተሳተፉ የተመራጮች ለውጥ ማድረግ የሚቻልበት ቀን በማለፉ በሂደቱ ላይ ለውጥ የለውም ብሏል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር እና ኢዜማ በክልሉ ምርጫ እንደማይሳተፉ ከቀናት በፊት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com