የእለት ዜና

በትግራይ ክልል የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ቦሎ ሊሰጣቸው መሆኑ ተገለፀ

በትግራይ ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በክልሉ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች የቦሎ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ባለማግኘታቸውና የተለያዩ አካላት ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ፤ ጊዜያዊ ፋይል በመክፈት ለ1 ዓመት የሚያገለግል ጊዜያዊ ቦሎ የሚሰጣቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ጊዜያዊ ፋይል በመክፈት ለ1 ዓመት የሚያገለግል ጊዜያዊ ቦሎ የሚሰጣቸው ተገልጋዮች፤ ከዚህ በታች የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት የሚገባቸው ሲሆን አገልግሎቱ፤ በየካ ክ/ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብቻ እንደሚከናወንም ተገልጿል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
-የባለቤትነት ማረጋገጫ ዋናውን እና ኮፒ ሊብሬ ማቅረብ

– ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ

– ተሽከርካሪው በአካል እና በባለቤትነት መታወቂው (ሊብሬ) ላይ ያለው የሻንሲ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎች ተመሳሳይ መሆናቸው ሲረጋገጥ

-ለኮድ 1 እና ለኮድ 3 ተሸከርካሪዎች ከሚመለከተው አካል ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ

-ሌሎች ለቦሎ አገልግሎት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ሰነዶች ሲሟሉ

እንዲሁም ባለንብረቱ ወይም ህጋዊ ተወካይ በጊዜያዊነት ለ1 ዓመት ብቻ ይህ የቦሎ አገልግሎት እንዲሰጠው የማመልከቻ ደብዳቤ ማቅረብ የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።

ከቦሎ አገልግሎት ውጪ ማንኛውንም አገልግሎት የማይሰጠው እንደሆነ ግንዛቤ ተወስዶ አገልግሎቱ እንዲሰጥ የፌደራል ትራንስፖርት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንዲከናወን እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ እያሟሉ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com