የእለት ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዩክሬኑ ሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳነት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና እና የሰሚ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶ/ር ቴትያና ሜይቦሮዳ የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነትና ትብብር ተባባሪ ዳይሬክተር ፈርመዋል፡፡

ስምምነቱ በጥናት ፣ በአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠናዎች፣ በሰራተኛና ተማሪዎች ልውውጥ፣ በዓለም አቀፍ የጋራ አጀንዳዎችና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።

ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎችተባብረው መስራት በሚችሉባቸው መስኮች ላይ አተኩረው ለመስራት ከመግባባት ላይ መድረሳቸው በስምምነቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

ስምምነቱ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን እንዳስፈላጊነቱ እየታየ የሚታደስ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com