የእለት ዜና

ለኹለት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የኢኑጉ በረራ ተጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፊት በረራ ያደርገበት የነበረውንና ለኹለት ዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ወደ ናይጄሪያ ኢኑጉ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው።
አየር መንገዱ በረራውን ካቋረጠ ከኹለት ዓመት በኋላ ጥቅምት 1/2021 ወደ ናይጄሪያ ምሥራቃዊ ዕምብርት በረራ ሊጀምር ነው።
በ 2019 የናይጄሪያ የአቪዬሽን ባለሥልጣናት የአውሮፕላን ማረፊያውን ለማደስ አየር ማረፊያዎቹን ሲዘጉ ወደ ኢኑጉ በረራ ተቋርጦ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ማረፊያው ከመዘጋቱ በፊት ወደ ኢኑጉ የሚንቀሳቀስ ብቸኛው ዓለም ዐቀፍ አየር መንገድ ነበር።
በሳምንት ሦስት ጊዜ የሚደረገው በረራ በቦይንግ 787 ድሪምላይነር አማካይነት ሲሆን፣ በረራዎቹ በየሳምንቱ ረቡዕ፣ አርብ እና ቅዳሜ አገልግሎቱ ይሰጣል።
የኢኑጉ አውሮፕላን ማረፊያ በፈረንጆቹ 2020 ለአገር ውስጥ በረራዎች እና በነሐሴ 2021 ደግሞ ለዓለም ዐቀፍ በረራዎች በይፋ መክፈቱን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀድሞ ወደ አካባቢው ለመብረር ዝግጅቱን አጠናቋል።
ጥቅምት 1 የናይጄሪያ የነጻነት ቀን ሲሆን፣ በዚያ ቀን ወደ ኢኑጉ መብረር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይጄሪያ ጋር ያደረገውን መልካም ግንኙነት ያጠናክራል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በናይጄሪያ አራት በረራዎች የሚያደርግ ሲሆን አቡጃ፣ ሌጎስ ፣ ካኖ እና ኢኑጉ ተጠቃሽ ናቸው።


ቅጽ 3 ቁጥር 151 መስከረም 15 2014

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com